የኤርትራ የልዑካን ቡድን በሐዋሳ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ ጎበኘ

የኤርትራ መንግሥት የልዑካን ቡድን በሀዋሳ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው ዕለት ጎበኘ ።

በኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዑስማን ሳልህ የተመራው ልዑክና የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ ሃዋሳ ከተማ ሲገቡ በደቡብ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎለታል።

የልዑካን ቡድኑ በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት ሲያደርግ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር በላቸው መኩሪያ ገለጻ ተደርጎለታል።

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በኢንቨስትመንት መስክ ያለውን ልምድ ለመቅሰም ያለመ ነው ተብሏል።

ኮሚሽነሩ የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በሃገሪቱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን በወቅት ተናግረዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በቅርቡ ኤርትራን አንደኛዋ የገበያ መዳረሻ እንደምታደርግም አንስተዋል።