በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቤተሙከራ የ19 አመቷ ኢትዮጵያዊት ጠበብት

የ19 አመቷ ኢትዮጵያዊት ቤተልሄም ደሴ ሼባ ቫሊ ተብሎ በሚጠራው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቤተሙከራ በምትሰራቸው ስራዎቿ "ወጣቷ ፕሮግራመር" ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

በአገራችን በማደግ ላይ የሚገኘው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከአይኮግ የሮቦት ቤተሙከራ ጋር በመሆን ሶፊያ የተሰኘችውን ሮቦት ግንባታን ጨምሮ በርካታ ስራዎች ላይ ተሳትፋለች፡፡

ቤተልሄም 4 የሶፍትዌር መተግበሪያዎን ሰርታ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያገኘች ሲሆን ከሰራቻቸው መተግበሪያዎች ውስጥ መንግስት የሚጠቀምበት የመስኖ አገልግሎት የሚሰጡ ወንዞችን በካርታ ላይ ለማመላከት የሚያስችለው መተግበሪያዋ አንዱ ነው፡፡

በሀረር ከተማ የተወለደችው ቤተልሄም ገና የ9 አመት ህፃን እያለች በአባቷ የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ውስጥ ቪዲዮ ኤዲት በማድረግና ለደንበኞች ሙዚቃ ወደ ስልክ በመላክ ገቢ ሲታገኝ እንደነበር ተገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በአይኮግ ስር ባለው ሶልቨኢት የተባለውን ፕሮጀክት ትመራለች፡፡

በ2006 ዓ.ም ወደ ስራ የገባው አይኮግ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስና ፕሮግራሚንግ በአገር ውስጥ የሚሰራው ስራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አመራር እያደገ መምጣቱን የሲኤንኤን ዘገባ አመላክተዋል፡፡