አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የስለላ ስራን አዳጋች እያደረጉ መምጣታቸው የእስራኤል ስለላ ደርጅት አስታወቀ

አዳዲስ የቴክኖሎጂ  ውጤቶች የስለላ ስራን አዳጋች እያደረጉ መምጣታቸውን የእስራኤል ስለላ ደርጅት አስታውቋል፡፡

ስለላን አዳጋች ካደረጉ የቴክሎጂ ውጤቶች ውስጥ የፊት ገጽታን መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ አንዱ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ቴክኖሎጂ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሲያመዝን የሚስተዋል ሲሆን ለዚህ ደግሞ እንደ ጥሩ ማሳያ የሚነሳው የፊት ገጽታን ማወቅ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ አንዱ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ወንጀለኞችን ለመለየት ያለው ፋይዳ የጎላ ባይሆንም ለሀገራቸው ጥቅም ሲሉ ወንጀል የሚሰሩ የደህንነት ባለሞያዎችን ሲያሳጣ ይስተዋላል፡፡

ከወደ እስራኤል የተሰማዉ ዜናም ይህንኑ የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የእስራል ብሄራዊ ደህንነት ሞሳድ ዳይሬክተር ጆሴፍ ኮሄንም የሰጡት መግለጫ ነው፡፡

ከስራቸው ባህሪ የተነሳ ለሚድያ ሩቅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዳይሬክተሩ ስለ ቴክኖሎጂ ጠቀሜታ እና ጉዳት ሲያውጉ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር በምናደርገው ጥረት ውስጥ የፊት ገጽታን እንደሚለዩ አይነት ቴክኖሎጂዎች ስራቸውን በአግባቡ ለማከናውን ፈተና እንደሆነባቸው ይገልጻሉ፡፡ 

የስለላ ስራ ከመቼም ጊዜ በላይ ፈታኝ እየሆነ መጥቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተመሳሳይ  ቴክኖሎጂን መጠቀም ይረዳ ይሆናል፤ ነገር ግን መሰል ቴክኖሎጂዎች የማንኛዉን ሀገር የደህንነት ስራተኞች ስራ ላይ የራሳቸውን ፈተና ደቅነዋል ነው ያሉት፡፡

በእየሩሳሌም  የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር ባዘጋጀዉ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዉ በቴክኖሎጂ የተነሳ የስለላ ስራ አዳጋች መሆኑን ያስረዱት ዳይሬክተር ጆሴፍ በዚህም ተነሳ የስለላ ስራ ችግር ዉስጥ መግባቱን ተናግረዋል፡፡

በምእራቡ ዓለም ከአሜሪካ የስለላ ደርጅት ሲአይ ኤ በመቀጠል ትልቁ  የስለላ ድርጅት እንደሆነ የሚነገርለት የእስራኤል ስለላ ደርጅት ሞሳድ የወቅቱን ፈተና ለመሻገር የተሻለ በጀቱን እና ፈንዱን በመመደብ ችግሩን መሻገር እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለዉም የእስራኤል ስለላ ድርጅት ሞሳድ በኢራን ኒዩክለርና ሚሳይል ፕሮጀክቶች  የሚደርሰዉን ዛቻ ለመቆጣጠር እና የፍልስጤም እስላማዊ ታጣቂ ወታደሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን አሁን አገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉ የፊት ገፅታን መለየት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የስለላ ሂደቱን አስቸጋሪ እያደረጉት እንደሆነም ነው ጆሴፍ ኮሄንም የገለፁት፡፡

እንዲህ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማንኛዉም ሰዉ ጥሩ የሚባሉ ቢሆንም ይህንን ለማይፈልጉ ሰዎች ግን የተለያዩ ትዕዛዞችን ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል ብለዋል፡፡

የሞሳድ ትልቁ ችግር የሰዎች ፓስፖርት በአይናቸው ብሌን፣ በእጃቸው አሻራ እና በፊት ገፅታቸዉ መለየት መቻሉ አሸባሪዎችን ለመቆጣጠር ያስቻለውን ያህል የስላላ ስራተኖችን ህይወት አደጋ ውስጥ እየጣለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የጸረ-ሽብር ዘመቻውን ትግል የሚያደናቅፍ እንደሆነ ጆሴፍ ኮሄንም ገልጻዋል፡፡

ለብነትን ለመከላከል የአስራኤል የደህንነት ባለሙያዎች በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሃማስ ከተፍኛ ወታደራዊ አመራሮችን እንደገደሉ የሚያሳይ መረጃ የተገነው በነዚህ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ከዛ በኋላ ማሌዢያ እና ቱኒዚያ በተመሳሳይ መልኩ የተገደሉ የሀማስ አመራሮችን ግን ማን እንደገደላቸው ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ይህ ሁኔታ ሞሳድ መሰል ቴክኖሎጂዎች በስላዮቹ ላይ የሚያሳድሩትን አደጋ ማለፍ የሚያስችል ቴክኖሎጅ መፍጠር ሳትችል እንዳልቀረ ሮይተርስ በዘገባው አማላክቷል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ውስጥ በሀማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ላይ የተፈጸመው ግድያ በወቅቱ እስሬኤልን ጥፋተኛ ማድረጉን እስራኤልን ክፉኛ ያበሳጨ ተግባር እንደ ነበር ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፤ ሮይተርስ)