ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማሳደግ የህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

በወርክ ሾፑ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን በማሳደግ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል በሚቻልባቸው አማራጭ ሀሳቦች ላይ የሚያተኩር ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ዓለም አቀፍ ወርክ ሾፑ "ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ልህቀት ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል  ነው  የሚካሄደው ፡፡

የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማዘመን ይረዳሉ የተባሉ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የተደረጉ የጥናት ውጤቶች በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ምሁራን ቀርበው ለውይይት ቀርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከሰልን ከሚጠቀሙ ሀገራት ብራዚል እና ናይጄሪያን በመከተል 3ተኛዋ ሀገር መሆኑዋን በውይይቱ በቀረበ በጥናት ተጠቁሟል፡፡

በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየአመቱ ለጤና እክል ይዳረጋሉ ተብሏል፡፡ ይህንን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ አማራጮች ለህብረተሰቡ ሊቀርቡ እንደሚገባ በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡