60 የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራንና ፀሐፊያን የሚሳተፉበት መድረክ መዘጋጀቱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ

 

በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ለሚገኘው የብሔራዊ የማህበረሰብ ተኮር የምክከር መድረክ አንዱ አካል የሆነ የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን እና ፀሐፊያን የሚሳተፉበት መድረክ ተዘጋጀ፡፡

የውይይት መድረኩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ፣ ዴስቲኒቲ ኢትዮጵያና ሀሴት የሳይኮ ቴራፒ ማዕከል የሚያስተባብሩት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በመድረኩ ላይ 60 የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራንና የታሪክ ፀሐፊያን እንደሚሳተፉበትም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ምሁራኑና የታሪክ ፀሐፊያኑ የተመረጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ አማካኝነት ሲሆን ተወያዮች በነፃነት ሃሳባቸውን የሚያንሸራሽበት መድረክ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ለ4 ቀናት በሚቆየው ውይይት በታሪክ አፃፃፍ እና በመሰረታዊ የታሪክ አረዳድ ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ውይይት እንደሚካሄድ  ተገለፀ፡፡

(ምንጭ፡-ኢዜአ)