8 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ 6ቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ስምንት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

በሕግ ማስከበር ስራው ስድስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና 87 ደጋፊዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ለሁለት ወራት በዞኑ በተደረገው የሕግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ 265 የኦነግ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱና የኦነግ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበረው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡