90 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና 8 ሺሕ 600 ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል መላካቸው ተገለጸ

ታኅሣሥ 15/2015 (ዋልታ) 90 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና ከ8 ሺሕ 600 ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል መላካቸውን የተባበሩት መንግስታት ገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያ ቢሮ በቲዊተር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የተለያዩ ነፍስ አድን እርዳታዎች እንዲሁም ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል በአራቱም አቅጣጫ እየተላከ ይገኛል፡፡

በዚህም ከአውሮፓዊያኑ ኅዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ታኅሣሥ 22/2022 ድረስ በአማራና በአፋር ክልል በአራቱም አቅጣጫዎች 90 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና 8 ሺሕ 600 ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን አመልክቷል፡፡