የግብርና ሚኒስቴር የግብዓት ስርጭትን በተመለከተ ውይይት እያካሄደ ነው

 

የግብርና ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማገዝ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ በሠፊው ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘውን የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሷደሮች ለማድረስ በሚሠሩ ተግባራትና እየገጠሙ በሚገኙ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ምክክር በባህርዳር እየተካሄደ ነው።

በግብርና ሚኒስቴር በተዘጋጀው መድረክ ላይ የግብና ግብአት ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አይናለም መልካሙ ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ የግብርና የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የግብአት አቅርቦት ዋና ተዋናይ የሆኑት ትራንስፖርተሮች፣ዩኒየኖችና መሠረታዊ ማህበራት የተሳተፉበት ነው።

በተለይም በአማራ ክልል የግብአት አቅርቦት ክፍተት፣ወቅታዊነትና የአርሶ አደሮች አጠቃቀም ውስንነት በምርታማነት ላይ ችግር መፍጠሩንም በመድረኩ ላይ ተመልክቷል።

የግብርና ሚኒስቴር ከግብርና የሥራ ኃላፊዎች፣ ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ አካላት፣ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ከሌሎች ባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለ2013/2014 የምርት ዘመን የሚውሉ የግብርና ግብዓቶች ለአርሶ አደሮች በወቅቱ በሚደርሱበት ሁኔታ ላይ በባሕር ዳር እየመከረ ነው።