የካቲት 4/2014 (ዋልታ) አገሪቱ የገጠማትን የኅልውና አደጋ ለመመከት የክልሉ ሕዝብ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው ገለጹ፡፡
የደቡብ ክልል መንግሥት የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በሀዋሳ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የሕዝቡን የቆዩ እሴቶች በመጠቀም የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሥራ በመሰራቱ በተነጻጻሪ ሲታይ ሰላማዊ ክልል መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት የተለያዩ የልማት ሥራ ግቦችን በበጀት ዓመቱ አስቀምጦ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አስታውሰው በዕቅዱ አፈጻጸም ሰፊ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመላክቷል።