ከ17 ሺህ በላይ የጤና ሰራተኞች በኮቪድ-19 ሕይወታቸው ማለፉ ተገለፀ

 

የካቲት 26/2013 (ዋልታ) – ባለፈው አንድ አመት በ70 አገራት ብቻ ከ17 ሺህ በላይ የጤና ሰራተኞች በቫይረሱ ህይዎታቸው ማለፉ ታውቋል።

የጤና ባለሙያዎች ባላቸው ተጋላጭነት ምክንያት የኮቪድ-19 ክትባቶች ቀድመው እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

በርካታ ሀገራት የሟቾችን ቁጥር ከመቀነስ ጀምሮ ጭራሹንም ሪፖርት የማያደርጉ መኖራቸውን በመግለጽ፤ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊልቅ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

በወረርሺኙ የሞቱ የጤና ባለሙያዎች አሃዛዊ የመረጃ ስሌት የሚያሳየው በየ 30 ደቂቃው አንድ ሰው ያልፏል፡፡

ይህም “አሳዛኝ እና ኢ-ፍትሃዊ” ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡

በተለይም በቫይረሱ ክፉኛ በተጎዱት በአሜሪካ (3 ሺህ 507)፤ በሜክሲኮ (3 ሺህ 371)፣በብራዚል (1ሺህ143) በሩሲያ እና በዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ 931 የጤና ባለሞያዎች እስካሁን ህይወታቸው አልፏል፡፡

እንደ አልጀዚራ ዘገባ 17ሺህ የጤና ባለሞያዎች ሞት አሃዛዊ መረጃ መንግስታት፣የሰራተኛ ማህበራት፣ሚዲያ እና የሲቪል ማህበራት ካሳተሟቸው መረጃዎች ላይ የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በእነዚህ ሀገራት ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሁኔታ እና የግል መከላከያ መሣሪያዎች እጥረት ባለሙያዎችን ለሞት ዳርጓል፡፡

ባለፈው አመት የኮቪድ 19 ስርጭት መከላከያ የህክምና መሳሪያ በ63 ከፍተኛ እጥረት ተመዝግቧል፡፡

ከነዚህ አገራት ውስጥም ማሌዢያ፣ሜክሲኮ እና አሜሪካን የሚገኙበት ሲሆን በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የፅዳትና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኖች የተሻለ የሥራ ሁኔታዎችን ከጠየቁ የመባረር እና የእስር እርምጃዎች ገጥሟቸዋል ነው የተባለው፡፡