ከተማ አስተዳደሩ በአፋር ክልል ለሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች የአይነት ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 23፣ 2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል ለሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች የተለያየ የምግብ አይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ከተማ አስተዳደሩ አሸባሪው የህወኃት ቡድን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቃጣውን የሽብር ተግባር ለመመከት ከህብረተሰቡ ያሰባሰበውን የተለያዩ ምግቦቸና ቁሳቁስ ለአፋር ክልል አስረክቧል፡፡
ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እና ለመላው የፀጥታ ሀይሉ ከተሰበሰበው ድጋፍ ለአማራ ክልል እና አፋር ክልል ለሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ከትናንት ጀምሮ በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ ነዋሪዎችና ባለሀብቶች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡