ከተማዋን ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን ስራ ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ


የካቲት 28/2016 (አዲስ ዋልታ) ሀረር ከተማን ለነዋሪው እና ለጎብኚው ምቹ ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን ስራ ማጎልበት እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የሀረር ከተማ ስትራቴጂክ የልማት እቅድ ለመምራት ከተቋቋመው ግብር ኃይል ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በወይይቱም ወቅት ሀረር ከተማን ውብና ጽዱ በማድረግ ለነዋሪውና ለጎብኚው ምቹ ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን ስራ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንንም ስራ ለማጎልበት በስትራቴጂክ እቅድ የታገዙ ስራዎችን ማከናወንና ለተግባራዊነቱም በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

በተለይ በክልሉ የመንገድ፣ የመብራት፣ ውሃ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ማስፋፋት እንዲሁም የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስራዎች ዘመናዊነትን የተከተለ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

በሆቴል፣ ትራንስፖርትና በሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋሟት የሚታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ የሚከናወኑትን ስራዎች ማጎልበትና ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህም ጎን ለጎን ለቱሪዙም ዘርፉ ውጤታማነት የሀረርን የእንግዳ ተቀባይነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እና የአብሮነት እሴት ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ግልጽ የሆነ ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባት አለበት ሲሉም አስገንዝበዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)