የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር በመሆን የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ

መኖሪያ ቤቶች ግንባታ

ሚያዝያ 19/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርኃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀመረ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ከ14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ህንጻዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ ለገባው ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከህግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል ሲሉም አክለዋል።