ሀገር በቀል የግጭት አፈታትና እርቀ ሰላም ዘዴዎች ዙሪያ ህዝባዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የግጭት አፈታትና እርቀ ሰላም ዘዴዎች ዙሪያ ህዝባዊ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ ከተለያዩ ክልል የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ሱራፌል እያጋጠሙ ያሉ ግጭቶችን መንግስት ብቻውን የሚውጣ ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ የሚያደርጉት ምክክርና ውይይት እያጋጠሙ ካሉ ችግሮች በስተጀርባ ያሉ መንስኤዎችን ለመለየት ብሎም መፍትሄ ለማስቀመጥ ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው በተሳታፊዎች በኩል የእርስ በርስ ትውውቅና ትስስር በመፍጠር መልካም ግንኙነት መፈጠሪያ አጋጣሚ መሆኑም ተመላክቷል።

መድረኩን እርቀ ሰላም ኮምሽን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይም ነው የተገለጸው።

(በደምሰው በነበሩ)