በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመተከል ዞንና ወረዳ ነባርና አዳዲስ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ፣ ሀገራዊና ክልላዊ ይዘቶች ያሉትና በቪዲዮ ተቀርፆ የቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መልእክትም ለሰልጣኞቹ ቀርቧል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ የስልጠና እና ሱፐር ቪዥን ዘርፍ ሃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ሞላ እንዳሉት በስልጠናው የመተከል ዞንና ወረዳ ነባርና ተተኪ አመራሮች ተሳትፈዋል።
የስልጠናው ዋነኛ አላማ በዞኑ የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችንና አጠቃላይ የአመራር ብቃት ክፍተቶችን ለመሙላት መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው አመራሮችም ከስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
ስልጠናው በዞኑ የሚታየውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እንደ አንድ መፍትሄ ይታያል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው፣ በተለይ አሁን እየመጡ ያሉ ተተኪ አመራሮች በህዝብ ይሁንታና ግምገማ የመጡ መሆናቸው ለአካባቢው መረጋጋት አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።