ለሚሊሻ የተሃድሶ እና የማነቃቂያ መርሃግብር

መስከረም 13/2013 (ዋልታ) – በወሎ ግንባር ተሰልፎ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እየተፋለመ ለሚገኘው ሚሊሻ የተሃድሶ እና የማነቃቂያ ዝግጅት ተካሄደ።

በማነቃቂያ መርሃግብሩ ላይ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ኤርሚያስ መኮንን የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን እኩይ ዓላማን ለማክሸፍ ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ተጋድሎና ጀብዱ እየተፈጸመ ነው ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል በርካታ ሕዝብ ለከፋ መጎሳቆል እንዲዳረግ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

በወራሪው ሃይል በሕዝብ ላይ እየደረሰ ካለው መከራና ስቃይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል በጽናት ታግሎ ሽብርተኛውን ቡድን ማጥፋት ይገባልም ብለዋል።

የሽብር ብድኑን ለማጥፋት ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ዋልታ ያነጋገርናቸው የሚሊሻ አባላት ተናግረዋል።
ሳራ ስዩም (ከወሎ ግንባር)
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!