በደሴ ለተፈናቀሉ ዜጎች የተደረገ ድጋፍ

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ለተፈናቃይ ዜጎች 26 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ አልባሳት፣ መገልገያ ቁሳቁስና ምግብን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሕይወት ኃይሉ እና የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ ድጋፉን ለደሴ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።
በተመሳሳይ ዜና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውለውን ድጋፍ የኢዜማ አመራርና አባላት በደሴ ትግል ፍሬ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተጠለሉ ዜጎች እንዲውል ማሰረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!