ለጀግኖቹ እነ እሸቴ ሞገስ የአስከሬን የክብር ሽኝት እየተደረገ ነው

ጥር 1/2014 (ዋልታ) የጀግናው እሸቴ ሞገስና የልጁ ይታገስ እሸቴን አስከሬን ከተቀበረበት ሳላይሽ ወጥቶ በሽዋሮቢት ቅድስት ማሪያም ቤቴክርስቲያን ለማሳረፍ የክብር አሸኛኘት እየተደረገ ነው።
ጀግኖቹ እሸቴ ሞገስና ልጁ ይታገስ እሸቴ ለአገር ነፃነትና ለወገን ክብር ሲሉ የትሕነግ ወራሪ ኃይልን በመፋለምና በትንሹ 9 አሸባሪዎችን በመግደል መስዋዕትነት የከፈሉ ናቸው።
አሁን ላይ በመኖሪያ ቤቱ ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የክብር አሸኛኘት እየተደረገለት ይገኛል።
አፅማቸው በትውልድ ቀያቸው እንዲያርፍ በሚል ነው የሽብር ቡድኑን ሲፋለሙ ከወደቁበት ሳላይሽ ወደ ሸዋሮቢት እንዲፈልስ የተደረገው።
ምንይሉ ደስይበለው (ከሸዋሮቢት)