ከዋሽንግተን ዲሲ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለሚያደርጉ አርቲስቶች ሽኝት ተደረገ

ጥር 1/2014 (ዋልታ) ከአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለሚያደርጉ አርቲስቶች ሽኝት ተደረገ፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ መቀጠሉን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለሚያደርጉ አርቲስቶች የአሸኛኘት ፕሮግራም መካሄዱን ገልጸዋል፡፡