ምርጫ አስፈጻሚዎች የእጩ ወኪሎች ባጅ የመስጠት ሥራን እስከ ነገ ማታ እንዲያጠናቅቁ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – የምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች የእጩ ወኪሎች ባጅ የመስጠት ሥራን እስከ ነገ ማታ (ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም) እንዲያጠናቅቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።

ሰኞ ሰኔ 14 ቀን ለሚከናውነው አጠቃላይ ምርጫ የፓርቲ ወኪሎችን እውቅና ባጅ የመስጠት ሥራ እያከናወኑ የሚገኙ የምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች ካለው አጭር ጊዜ አንጻር የእጩ ወኪሎች ባጅ መስጠቱን ከላይ እስከ ተጠቀሰው ጊዜ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ መቅረቡን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።