ቻይና ከ100 ሺህ በላይ የኮቪድ 19 ክትባት ለኢትዮጵያ አስረከበች

ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – የቻይና መንግስት ከ100 ሺህ በላይ የኮቪድ 19 ክትባት ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክቧል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ጀረጀ ድጉማ የቻይና መንግስት  ኢትዮጵያ ወረርሽኙን የመከላከል ስራዋን አጠናክራ እንድትቀጥል በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥዋን ዚዊን ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 የመከላከል ስራ አጠናክራ እንድትቀጥል የቻይና መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው 40 ሺህ የሚሆነውም ክትባት ለትግራይ ክልል ይሆናል ብለዋል፡፡

(በዙፋን አምባቸው)