ምክር ቤቱ የነጃሺ ታሪካዊ መስጂድ በደረሰ ጥቃት ጉዳት መድረሱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የዓለም ቅርስ በሆነው የነጃሺ ታሪካዊ መስጂድ እና የቀብር ቦታ በከባድ ጦር መሣሪያ በደረሠ ጥቃት ጉዳት እንደደረሰ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

በታላቁ የነጃሺ መካነ ቅርስ መስጂድ ላይ የደረሠውን ጥቃት አስመልክቶ ምክር ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ ሼህ ቃሲም ሙሓመድ ታጁዲን በመግለጫቸው ምክር ቤቱ በደረሠው ጥቃት ማዘኑን ገልጸዋል፡፡

ተግባሩ አጸያፊና አሳፋሪ ወንጀል በመሆኑ መንግስትና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ወንጀለኞችን በአፋጣኝ ለፍትህ እንዲያቀርቡ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

መንግስት ጉዳቱን በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ እና ማብራሪያ እንዲሠጥበት በመግለጫው ተነስቷል፡፡

(በሰሎሞን በየነ)