ሮቦት እና ሰዎች የተሳተፉበት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፊልም ተመረቀ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰዎኛ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ያቀረበው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

በመርኃግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ምድር የተሰሩ ሮቦቶችን በማሳተፍ ቀዳሚ የሆነ ፊልም እንደሆነም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ኢትዮጵያን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ መፍጀቱን አመልክተዋል።

“አስተውሎት” ፊልም በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሳይንሳዊ ፊልም ሲሆን በሚካኤል ሚሊዮን ተዘጋጅቶ ተፈሪ ዓለሙ እና ሀረገወይን አሰፋን ጨምሮ አንጋፋና ወጣት ተዋንያን የተሳተፉበት መሆኑም በመርኃግብሩ ተገልጿል።

 

በአማረ ደገፋው