ጀርመን 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ዋጋ ያለውን የሕክምና ቁሳቁስ ለሆስፒታሎች ድጋፍ አደረገች

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የጀርመን መንግሥት በጀርመን ልማት ባንክ አማካይነት ለስምንት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ዋጋ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝይድ ሆስፒታል፣ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አዳማ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከል፣ አይደር ሪፈራል ሆስፒታልና ለአርባምንጭ ሪፈራል ሆስፒታሎች ነው የተደረገው፡፡

ከቁሳቁስ ድጋፉ በተጨማሪ ለሆስፒታሎቹ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

ጀርመን በቀጣይም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡