በሀገሪቱ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሕጎች በአግባቡ ተሰንደው ተቀምጠዋል – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

የካቲት 22/2013 ዓ.ም (ዋልታ)፡- በሀገሪቱ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መመሪያዎች፣ ሕጎችና ደምቦች በአግባቡ ተሰንደው ተቀምጠዋል ሲሉ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ፡፡

የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል ሃሳብ የሴቶች የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሚኒስትሯ በዚህ መድረክ ላይ እንደተናገሩት እነዚህን በአግባቡ በመጠቀም ሴቶች ለሀገራዊ ብልጽግና ተግተው ሊሠሩ ይገባል፡፡

ሴቶች በማኀበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መጠናከር አለብን ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የአድዋ ድል በዓልን የሚዘከር ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል ሲል የዘገበው አብመድ ነው።