በመዲናዋ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች የተጀመሩ የኮንስትራክሽን ስራዎችን እየጎበኙ ነው

መጋቢት 22/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች አባላት በከተማዋ የተጀመሩ የኮንስትራክሽን ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገር በቀል ተቋራጮችን ከማሳተፍ እና የፕሮጀክቶችን የጊዜ ገደብ መጓተት አንፆር  ከፓለቲካ ፓርቲ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ  ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በሀገሪቱ ያለውን  የዶላር እጥረት ምክንያት አድርጎ ዝምታን ከመምረጥ ፣ የእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግርን መሰረት በማድረግ  እንዲሁም በራሳቸው የዶላር  በጀት መስራት የሚችሉ አለም አቀፋ ተቋራጮችን በማሳተፍ ስራው እንዲቀጥል ተደርጓል ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ።

በኮንስትራክሽን እቃዋች የዋጋ ጭማሪ እና በኮቪድ ወረርሽኝ የተከሰተውን የእንቅስቃሴ መገታት እና ሌሎች ምክንያቶችን ተከትሎ የተከሰተውን መጓተት በመቅረፍ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ እቅድ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ እየሰራን ነው ብለዋል።

ከሰባት የሚበልጡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መኖራቸው በጉብኝቱ ወቅት የተገለፀ ሲሆን  ከጊዜ ወደ ጊዜ የስራውን ሂደት በማፋጠን እና ለሚገጥሙ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት  እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(በቁምነገር አህመድ)