በመጋቢት ወር ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት ከ107 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ሚያዝያ 04/2013 (ዋልታ) – በመጋቢት ወር ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት ከ107 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ገቢው በወሩ ወደ ተለያዩ አገራት ከተላከው 27 ሺህ 200 ቶን ቡና መሆኑ ታውቋል፡፡

በዚህም የተገኘው የውጭ ምንዛሪ እስከ አሁን ድረስ በአንድ ወር ውስጥ ተገኝቶ የማያውቅ ገቢ ነው ተብሏል፡፡

ይህም በዋነኝነት ላኪዎች ቡናን በቀጥታ ትስስር ከአቅራቢዎች እና ከአርሶ አደሮች እንዲገዙ የማድረግ ስርዓት ተዘርግቶ የእሴት ሰንሰለቱ እንዲያጥር በመደረጉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ባለስልጣኑ በቅርቡ የቡና ግብይቱን የሚያሳልጡ የተለያዩ አሰራር ስርዓቶች መዘርጋቱ እና ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡