በማሌዢያ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት  የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ

ታኅሣሥ 7/2015 (ዋልታ) በማሌዢያ የመጠለያ ካምፕ ላይ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ17 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል፡፡

አደጋው ከዋና ከተማዋ ኩዋላ ላምፑር በስተሰሜን 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ካምፕ የደረሰ ሲሆን በግምት 94 ማሌዥያውያን ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም የ16 ሰዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ የአምስት አመት ህጻንን ጨምሮ ሌሎች 7 ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ከ17 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች እስካሁን የገቡበት ያልታወቀ ሲሆን 53 ሰዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣታቸውም ተገልጿል፡፡

የአካባቢው ፖሊስ በበኩሉ የጠፉትን ሰዎች ለመፈለግ የሰለጠኑ ውሾችን ጨምሮ ከ400 በላይ ሰራተኞችን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡