በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ታንዛንያ ገባ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ታንዛንያ ገባ

 

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ታንዛኒያ ገብቷል፡፡

ልኡካን ቡድኑ ጁሊዬስ ኔሬሬ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የታንዛኒያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ምባሮክ ኤን ምባርክና በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ልኡካን ቡድኑ ወደ ታንዛኒያ ያመራው ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው የአፍሪካ የሰው ሃብት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡