በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ለተፈናሉ ዜጎች 1.5 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

ሰኔ 01/2013 (ዋልታ) – በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጋጥሞ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነርና የየእርዳታ አሰባሳቢ ዓብይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዘላለም ልጃለም ከሁለቱ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ246 ሺህ በላይ መሆኑን ገልጸው፣ 3 ሺህ ቤቶች መቃጠላቸውን አስታውቀዋል፡፡

የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ዜጎችን ማቋቋም እንዲቻል ሁሉም ባለውና በቻለው መጠን ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚደረግባቸው የባንክ ቁጥሮችም ይፋ የሆኑ ሲሆን፣ በዚህም፡-

-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000399788181

-አቢሲኒያ ባንክ 66956466

-አባይ ባንክ 2012117396084010

-ዳሽን ባንክ 5020809534011

-ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ  1079601001041

-ህብረት ባንክ 2210411629526018

(በአመለወርቅ መኳንንት)