በሱዳን ያሉ ዜጎችን ደህንነት በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል- አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

ሰኔ 14/2015 (ዋልታ) በሱዳን ያሉ ዜጎችን ደህንነት በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡

በዛሬው ዕለት በሱዳን ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የተቋቋመ አገራዊ ግብር ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ያካሄደውን ስራ ገምግሟል።

በግምገማው ላይ ግብር ኃይሉ እስካሁን በተገኙ ውጤቶች እና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ዝርዝር ውይይት ማካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የግብር ኃይሉ ሰብሳቢ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በሱዳን ያሉ ዜጎቻችንን ደህንነት መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን በመድረኩ የተለያዩ የግብር ኃይሉ አባላት በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሪፖርት አቅርበዋል።