በቀጠናው ላይ መረጋጋትና ብልጽግናን የሚያስፋፉ የጠ/ሚ ዐቢይ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ እተማመናለሁ – ሴናተር ጂም ኢንሆፌ

 

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – በቀጠናው ላይ መረጋጋትና ብልጽግናን የሚያስፋፉ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ እተማመናለሁ” ሲሉ አሜሪካዊው ሴናተር ጂም ኢንሆፌ አስታወቁ።

ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

ሴናተሩ አያይዘውም፤ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ተደራሽ ለማድረግ ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች እንዲገቡ በማድረግ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትልቅ የሚባል እርምጃዎችን መውሰዳቸውን እና በዚህም እንደተደሰቱ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያ ትክክለኛ የለውጥ መሪ መሆናቸውን መመልከታቸውን ሴናተሩ አስታውቀዋል።

“በቀጠናው ላይ መረጋጋትና ብልጽግናን የሚያስፋፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ እተማመናለሁ” ሲሉም ነው ሴናተር ጂም ኢንሆፌ የገለጹት።