በተጠባቂው የለንደን ማራቶን የ41 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ በሁለተኝነት አጠናቀቀ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

ሚያዚያ 13/2016 (አዲስ ዋልታ) የ41 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ርቀቱን 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ15 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ወጥቷል።

ውድድሩን በአንደኝተት ያጠናቀቀው ኬንያዊው አሌካሳንደር ሙቲሶ ሲሆን ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ01 ሰኮንድ ወስዶበታል።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ

በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ ወድድሩን 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ23 ሰኮንድ በመጨረስ ሁለተኛ ስትሆን ኬንያዊቷ ፕሬስ ጀብችርችር ርቀቱን 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ16 ሰኮንድ በመሮጥ አንደኛ መውጣቷን ኤንቢሲ ስፖርት ዘግቧል።

በሌላ በኩል አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 የማራቶን ውድድርን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡