ሰኔ 23/2013(ዋልታ) – የተኩስ አቁም ስምምነቱ በትግራይ ክልል በአሸባሪው የህወሃት ቡድን እየተፈፀመ ላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሰበብ ላለመሆን እና አርሷአደሩ የሰብል መሰብሰቢያ ጊዜን እንዲጠቀም በማሰብ የተወሰነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።
ቡድኑ በኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የሚወሰድበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ በህዝቡ ዘንድ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት እንዲሸበርና ለሠራዊቱ ያለው አመለካከት በጥርጣሬ የተሞላ እንዲሆን ሲሰራ ነበር ሲሉ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ተናግረዋል።
(በአስታርቃቸው ወልዴ)