በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ ተጀመረ

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ መጀመሩን የብሄራዊ ባንክ አስታወቀ::

የብር ቅያሪው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡