በንግድ ማስፋፊያ የስራ ዘርፍ ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ኮቪድ-19 በንግድ ማስፋፊያ የስራ ዘርፍ የጋረጠባቸው ፈተናዎች እና ያሉ ተስፋዎች ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

የንግድ ስራን ውጤታማ ለማድረግ አንዱ የሆነው ንግድና ባዛር ሁነት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ በኢትዮጵያ በዘርፉ ተዋናይ የሆኑ 700 ሁነት ፈጣሪ ድርጅቶች ስራቸውን አቁመው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ለስራአጥነት ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል።

በንግድ ስራ ማስፋፊያ ዘርፍ ያለው የማስተዋወቅ ተግባር በንግድና ባዛሮች ላይ በዘርፉ የእውቀት ውስንነት፣ ለንግድና ባዛር አመቺ የመሠረተ ልማት አለመኖር፣ ወጥ ህግና መመሪያ አለመኖር፣ ለድርጅቶች ማበረታቻ አለመኖር እና ሌሎችም ምክንያቶች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ ዘርፉን መጉዳቱና ለሀገሪቱ ማስገባት ያለበትን ገቢ ማሳጣቱ ተነግሯል።

(በምንይሉ ደስይበለው)