በአፍሪካ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንዳልሆነና መዘናጋቱ እየተባባሰ መምጣቱን ጥናት አመለከተ

ኮቪድ-19

መጋቢት 16/2013 (ዋልታ) – በአፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የኮቪድ-19 ስርጭት ቢኖርም፤ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንዳልሆነና መዘናጋቱ እየተባባሰ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

በ’ላንሴት ሜዲካል ጆርናል’ የወጣ መረጃ በአፍሪካ የኮቪድ-19 ጥንቃቄ ርምጃዎች መዘንጋታቸውንና መጀመሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲከሰት የነበረው የጥንቃቄ እርምጃ የተሻለ እንደነበር ጠቁሟል።

ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካኝ 18 ሺህ 273 እንደነበር አስታውሶ፣ በአሁኑ ወቅት በቀን በአማካኝ ወደ 23 ሺህ 790 ከፍ ማለቱን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ጆርናሉ ባለፈው አመት የኮቪድ-19 በተከሰተበት የመጀመሪያ ወራት የነበረው ጥንቃቄ አሁን መዘንጋቱን ያለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የነበረውን ሁኔታ በአብነት ጠቅሶ መዘናጋቱ እንደተባባሰ ገልጿል።

በሚያዚያ ወር የነበረው ጥንቃቄ 96 በመቶ ከነበረበት ደረጃ ከ11 ወራት በኋላ ወደ 72 በመቶ ዝቅ እንዳለ መጥቀሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡