በኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍ ረቂቅ ሰነዶች ዙሪያ ግምገማ ተደረገ

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍ የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕውቅና አሰጣጥ ረቂቅ ሰነዶች ግምገማ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)  ሰነዶቹ  የትምህርት ጥራትና አግባብነትን በሚመለከት ከህዝቡ እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ይፈታሉ ብለዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉ ነጋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ባለፉት ዓመታት በትምህርት ተደራሽነት እና ፍትሃዊነት ላይ የተሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

መርኃግብሩ ከመስከረም 13 እስከ 14 ለሁለት ቀናት የተዘጋጀ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡