በኢትዮጵያ እየደረሠ ያለውን ጫና በተመለከተ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በሚል የተቃውሞ እንቀስቃሴ እየተደረገ ነው

ግንቦት 13/2013 (ዋልታ) – ብሄራዊ ክብር ለህብር በተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና በተመለከተ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በሚል መሪ ሃሳብ የተቃውሞ እንቀስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 10 ሰዓት ሁሉም ኢትዮጵያዊ “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ” በማለት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተቃውሞውን እንዲገልፅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የብሄራዊ ክብር ለህብር አስተባባሪ አብይ ታደለ ሁሉም ለሀገሩ ያገባኛል የሚል እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ገልጸው፣ ከሲቪል ማህበራት፣ ከኃይማኖት ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን ፍሬያማ የሆነ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ኤምባሲዎች ዛሬ ባለመስራታቸው አልተሳካም ብለዋል።

(በመስከረም ቸርነት)