በኦሮሚያ 4.4 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ተገለጸ

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በኦሮሚያ ክልል 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡
የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በስፋት እየተሰራበት ይገኛል፤ በዘንድሮው አመት 4 ነጥብ 5 ቢልየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ ፣4 ነጥብ 4 ቢልየን ችግኝ ለማዘጋጀት ችለናል ብለዋል::
ይህም ከተያዘው እቅድ 96% የተሳካ ሲሆን የመሬት ዝግጅትን በተመለከተ በክልሉ 2 ነጥብ 6 ቢልየን ጉድጓድ ተቆፋሯል ብለዋል።
በችግኝ ተከላ መርሀግብሩ ላይ 13 ነጥበረ 9 ሚሊየን ህዝብ በ3 መርሀ ግብር ተሳታፊ ይሆናል ያሉት አቶ ዳባ በመርሀ ግብሩ በአንድ ቀን ከ 350 ሚሊየን በላይ ችግኝ ይተከላልም ብለዋል።
የመኸር እርሻን በተመለከተ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት ፣ የኤክስፓርት አቅምን ለመጨመር እና በክልሉ የስራ ፈጠራን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር የሚታረስ መሬት ውስጥ 4 ነጥብ 4 ሚልየን ሄክታር መታረስ መቻሉን ገልፀዋል።
ምርት እና ምርታማነትን ለመጨመር የክላስተር አሰራር በክልሉ በስፋት እየተተገበረ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳባ በዚህም 300ሺህ ሄክታር መሬት የክላስተር እርሻ ትስስር ተሰርቷል ብለዋል።
በክልሉ 1ሚሊየን የምርጥ ዘር ዝግጅት እቅደሰ ታቅዶ 661ሺህ የተዘጋጀ ሲሆን ፣አግሮ ኬሚካልን በተመለከተ 3 ሚሊየን ሊትር ለገበሬው ተደራሽ ሆኗል ተብሏል።
የቡና እና አትክልት እና ፋራፋሬ ምርት በዚህ አመት በኦሮሚያ ክልል ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ሲሆኑ የቡና የዘር ዝግጅት ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 1 ቢልየን ችግኝ ተዘጋጅቶ 800ሺ የቡና ጉድጓድ ተቆፋሯል።
በፋራፋሬው ዘርፋ አቮካዶ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ታቅዶ 1 ነጥብ 4 ግራፋት ተደርጓል ተብሏል።
ሙዝ ፣ፓፓያ እና የማንጎ ምርቶችን በማህበረሰቡ ዘንድ ተደራሽ በማድረግ በስፋት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስመጣቷ ለጉዳት ዳርጓታል ያሉት አቶ ዳባ ደበሌ የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ ይህንን ታሪክ ለመቀየር የስንዴ ምርት በክልሉ በስፋት እየተሰራበት እንደሆነ ነው ገልፀዋል።
(በቁምነገር አህመድ)