የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2014 ረቂቀ በጀት ላይ እየተወያየ ነው

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ አመት 15ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2014 ረቂቅ በጀት ላይ እየተወያየ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የፌደራል መንግስት የ2014 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ የበጀት መግለጫ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ በቀረበለት የበጀት መግለጫ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል።