በዞኑ 33 የኦነግ ሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ግንቦት 18/2014 (ዋልታ) 33 የኦነግ ሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አህመድ አሊ ገለጹ፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ተጠርጣሪዎችን ለይቶ ለሕግ ለማቅረብ ከኅብረተሰቡ ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም በዞኑ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ገልጸዋል።

በሕግ ማስከበር ዘመቻው ንፁሃን ያለአግባብ እንዳይያዙ በጥንቃቄ እየተሠራ እንደሚገኝም ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የተጀመረው የሕግ ማስከበር ተግባር ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡