በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ

ታኅሣሥ 11/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ፡፡

ቦርዱ በክልሉ በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሳኔ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በዛሬው ዕለት የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አመልክቷል፡፡

ለሕዝበ ውሳኔው በሚያገለግሉ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች 31 የሕዝበ ውሳኔ ማስተባበሪያ ማዕከላትና 3 ሺሕ 752 የምርጫ ጣቢዎች ማደራጀቱንም ቦርዱ አስታውቋል፡፡

ሕዝበ ውሳኔውን የሚያስተባብሩ በየደረጃው የሚገኙ ገለልተኛ 11 ሺሕ 429 አስፈፃሚዎች ተመርጠው እና ውል ገብተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ጠቁሟል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth