በጅግጅጋ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነቡ ት/ቤቶች ተመረቁ

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያስገነባቸውን የኢሌስ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የቀዳማዊት እመቤት በትምህርት ቤት እጥረትና እርቀት ምክንያት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ላልላኩ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ አጠቃላይ 27 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ወጪ ተደረገባቸው ሲሆን በአንድ ዓመት ጊዜ መጠናቀቃቸው ታውቋል፡፡

ት/ቤቶቹ ከ4ሺህ በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ሲኖራቸው፣ የመማሪያ ክፍሎችን፣ የአስተዳደር ብሎኮችን፣ የቤተ-መጻሕፍት እና የምርምር ቤተ-ሙከራዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቃቸው 8ኛና 9ኛ ትምህርት ቤቶችን ሲሆን በተያዘው አመት ግንባታቸው የተጠናቀቁ 10 ትምህርት ቤቶችን በሁሉም ክልሎች የሚያስመርቅ መሆኑን ከቀዳማዊት እመቤት በጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።