በጎፋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ድጋፍ መርሃግብር ተከናወነ

በጎፋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ድጋፍ

ግንቦት 02/2013 (ዋልታ) – በጎፋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ድጋፍ መርሃግብር ተከናወነ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መርሃግብር መሠረት የ6ኛ ብሔራዊ ምርጫ ተሳታፊ የሆኑ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛል፡፡

ይህንን ተከትሎ የብልፅግና ፓርቲ ከጎፋ ዞን ሴቶች ሊግ ጋር በሳውላ ከተማ ”ብልፅግና ለሁሉም ሴቶች ሁሉም ሴቶች ለብልፅግና” በሚል ድጋፍ ተከናውኗል፡፡

የዞኑ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ንጉሤ በምርጫ ዜጎች በተለይም የሴቶች ተሳታፊነት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ድምፅ በመስጠት ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መስፍን ስለሺ በበኩላቸው፣ የዘንድሮ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡