ቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ የእንቦጭ ማስወገጃ ማሽን ድጋፍ አደረገ

ሚያዝያ 11/2013 (ዋልታ) – ቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ ጣና ሀይቅ የወረረውን እንቦጭ አረም ለማስወገድ የሚረዳ ማሽን ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስረከበ።

በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተዘጋጀው የእንቦጭ አረም ማጨጃና ማስወገጃ ማሽን ርክክብ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናትና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በማክሰኝት ከተማ ተከናውኗል።

የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አያሌ ወንዴ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ግንኙነት ያለው የጣና ሀይቅ በዙሪያው ለሚኖሩ አርሶ አደሮች የህልውና መሰረት መሆኑን ጠቁመው፣ አረሙን ለማጥፋት ርብርብ ማድረግ ተገቢነት እንዳለው ገልፀዋል።

የቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረስላሴ ስፍር በበኩላቸው፣ ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበረሰባዊ ሀላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
(በዙፋን አምባቸው)