ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።
ገቢው የተገኘው ከ4112 ኪ.ግ በላይ ወርቅ፣ 26.97 ቶን ታንታለም፣ 1625 ኪ.ግ ጥሬ ኦፓል 37.8 ኪ.ግ እሴት የተጨመረበት ኦፓል እና 2123 ኪ.ግ ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት ለውጭ ገበያ ማቅረብ በመቻሉ መሆኑ ተገልጿል።
ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪ እና የኮንስትራክሽን ማዕድናት 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ተናግረዋል።
በዘርፉ ለ48 ሺህ 785 ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎች እና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አቅጣጫዎች ማስቀመጡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።