ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የእስራኤልን አምባሳደር አነጋገሩ

ሚያዝያ 04/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ የእስራኤልን አምባሳደር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ነው የተወያዩት።

ቅዱስነታቸው ከአምባሳደሩ ጋር በኢትዮጵያና በእስራኤል ዘመን የተሻገረ የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይም መክረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ በኢየሩሳሌም በሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት ዙርያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትም ተወያይተዋል፡፡