ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው ጋር ተወያዩ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በቅርቡ በነጃሺ በደረሰው ጥቃት ዙሪያ  ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም የምክር ቤቱን ባለሙያዎች ያካተተ በነጃሺ ቅርስ ላይ ስለደረሰው ጉዳት የሚያጠና ቡድን በአስቸኳይ ለመላክ መስማማታቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚያም ባለፈ በሌሎች እስላማዊ ቅርሶች ላይ የተሻለ አጠባበቅ እና ልማት ስለሚደረግባቸው መንገዶች በዝርዝር መወያየታቸው ተገልጿል።