ኡጋንዳ ለምታካሂደው ምርጫ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ዘጋች

ኡጋንዳ ነገ ለምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሁሉንም የማኅበራዊ ሚዲያዎች እና የመልዕክት መላላኪያ አማራጮች እንዲዘጉ አዘዘች፡፡

የኡጋንዳ ኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አይሪን ሴዋንካምቦ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የማኅበራዊ ሚዲያዎችን እና ማንኛውንም የመልዕክት መላላኪያ አማራጮች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆርጡ ትላንት ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

እገዳው የተላለፈው ኡጋንዳ ከምታካሂደው ምርጫ በፊት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በቅድመ ምርጫ ያሉ የክርክር ሐሣቦች ለመንግስት ወገነተኝነት ያላቸው እና አወዛጋቢ የሆኑ መረጃዎችን በማውጣታቸው አካውንቶቹ ሊሰረዙ መቻሉ ታውቋል፡፡

በኡጋንዳ የማህበራዊ ሚዲያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ ተጠቃሚዎች የግል ኔትዎርክ ወይንም የቪፒኤን አማራጮችን እየወሰዱ መሆኑን ኤኤፍፒ ገልጿል፡፡

ከ1986 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በ2017 የፓርላማ አባል ከሆኑት ድምፃዊ ሮበርት ካያጉላኒይ ጋር ይወዳደራሉ፡፡